Sale!

የአባት ዕዳ

መደብር

Original price was: Br 80.00.Current price is: Br 20.00.

የሰው ልጅ በሚራመድበት የሕይወት ጎዳና ውስጥ ከመልካምና ከመጥፎ ገጠመኞች ጋር ግብግብ መግጠም የሰርክ ሁነቱ ነው። ነገር ግን መጥፎ የሕይወት አጋጣሚዎችን እንዴት በብቃትና በብርታት ድል ማድረግ ይኖርበታል ። ካልተሳካ ከመረታት ብርታትና ትምህርትን መቅሰም ይኖርበታል። ምክንያቱም ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ትልቅ ትምህርት አለ ።

SKU: 66834 Categories: , ,

Description

ከመፅሐፉ የተወሰደ
… አካባቢው ፀጥ ብሏል፡፡ ዛፎቹን የሚያንኮሻኩሻቸው ንፋስ አካባቢውን ቀዝቀዝ አድርጎታል፡፡ አልፎ አልፎ የዝንጀሮዎች ጩኸት ይሰማል፡፡ ለተራራው ግርማ ሞገስ የሆነው ዋርካ ቅርንጫፍን አንዘራፍታል። ገለታ ከዋርካው ስር እየተንቀጠቀጠ ቁሟል፡፡ ሻላዬ መሬቱ ላይ ተኝታለች፡፡ የጎሳዋ ነዋሪዎች ፊት ለፊት ቁመዋል፡፡ ከመካከላቸው አንድም ኮሽታ አይሰማም፡፡ ሁሉም ፀጥ ብለዋል፡፡ በዝምታ መካከል ትንሽ አንደቆዩ ለንግግር የሚፈጥነው ሽማግሌ «ስራችን እንጀምር» በሚል አንድምታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡ በቅፅበት ወንዶች ከሴቶች ተለይተው ለብቻ ቆሙ፡፡ ሴቶች ለብቻ ሆኑ፡፡ ህፃናት የገለታንና የሻላዬን ስቃይ እንዲመለከቱ ፊት ቆሙ።
ሴቶች ሻላዬን እንዲገድሉ ከተናጋሪው ሽማግሌ ትዕዛዝ መጣ፣ የጎሳዋ ሴቶች ግን ፊታቸው ጠቆረ። የሽማግሌውን ትዕዛዝ በጉርምርምታ አወገዙት። ጉርምርምታው ቃል ወልዶ «በጭራሽ አናደርገውም።» በማለት አመፁ። የሴቶቹን እንቢተኝነት የተመለከተው ሽማግሌ ወደ ሴቶቹ አፍጥጦ «አንድም ሴት ለትዳሯ ታማኝ አለመሆኗን እያሳያችሁን ነው፡፡ ስለ እውነት ልንገራችሁ ለእነዚህ ሰዎች አዝናችሁ አይደለም፡፡ እናንትም ላይ አንድ ነገር ስላለ በመስጋት ነው፡፡ አሁን የተባላችሁትን ካልፈፀማችሁ ማንም ወንድ ከእናንተ ጋር አይጠጋም፡፡ ያለ ትዳር፣ ያለ ቤት ትኖራላችሁ፡፡ ይህን የሚፈቅድ ካለ ትዕዛዛችንን መጣስ ይችላል፡፡» በማለት በንዴት አፈጠጠ። ሴቶች በፍርሃት ውስጣቸው ተፈራገጠ፡፡ ሰብዓዊው ህሊናቸው ተሟገታቸው። አናደርገውም ቢሉ ቤት፤ ትዳራቸው ከፊታቸው ቆመ፡፡ ህሊናቸው ለሻላዬና ለቤት፣ ትዳራቸው ተጨነቀ፡፡ በጭንቀትና በውጥረት እንደቆዩ አንድ ሁለት ድንጋዮች ከሴቶች እጅ መወርወር ጀመሩ፡፡ ቀስ በቀስ ሴቶች ሁሉ እጃቸው የሞላውን ድንጋይ አንስተው ወደ ሻላዬ በመወርወር ድንጋይ አዘነቡባት። በድንጋይ ተቀጥቅጣ እንድትገደል ተደረገ፡፡ አንድም የጎሳዋ ሴት ያልወረወረች ሳትገኝ ሻላዬ በሴቶች ተገደለች፡፡
ገለታ በሻላዬ የደረሰው ጭካኔ አሳዘነው፡፡ ያለ በደሏ እንዲህ ተቀጥቅጣ ስትገደል ውስጡ ተንሰፈሰፈ። ለራሱ ሳይሆን ለሻላዬ አነባ፡፡ ለራሱ ሳይሆን ለሻላዬ አዘነ፡። ከአውሬ ጋር የታገሉት ክንዶቹ የታሰረበትን ገመድ መበጠስ አቃታቸው፡፡ አቀበቱንና ቁልቁለቱን ያለድካም የገሰገሰባቸው ፈርጣማ ታፋዎቹ ማምለጥ ተሳናቸው፡፡ ትንሽ እንደቆየ ጉተማ ፊት ለፊቱ ሲመጣ ተመለከተው፡፡ ገመዱን ለመበጠስ ታገለ። ገመዱ በህይወቱ ላይ ፈረዶ አልበጠስ አለው፡፡
ጉተማ ወደ ገለታ በመጠጋት በምፀት ከተመለከተው በኋላ መርፌ የበዛበትን የገለታን ቁምጣ አውልቆ በያዘው «ቢላዋ» እፍረት ስጋውን ቀነጠሰው፡፡ ገለታ እፍረት ስጋው ሲቆረጥ ከባድ ጩኸት በማሰማት መሬት ላይ ተንበረከከ፡፡ ጉተማ የቆረጠውን እፍረተ ስጋ ከፍ አድርጎ ለህዝቡ አሳዬ። ወንዶች በደስታ ቦረቁ፡፡ ሴቶች አንገታቸውን ደፉ። ቀጥሎም ወንዶች የጉተማን ቢለዋ ተራ በተራ እየተቀበሉ ሰውነቱን በሙሉ ተለተሉት። በመጨረሻም ጉተማ ወደ ገለታ በመጠጋት እፍረተ ስጋውን በቆረጠበት ቢላዋ አንገቱን ቆርጦ ጭንቅላቱን ከሰውነቱ በመለየት ወደላይ ከፍ አድርጎ ለህዝቡ አሳየ፡፡ ነዎሪዎቹም በደም ሰክረው ጨፈሩ። ደስታቸውን በጩኸት አሰሙ፡፡ ትንሽ ቆይቶም ህፃናት አድገው የሰው ትዳር እንዳያፈርሱ፣ የባለትዳር ሚስቶችን እንዳያማግጡ ትምህርት እንዲሆናቸው ለማድረግ የተጨፈላለቀውን የሻላዬን እና ጭንቅላት አልባ የሆነውን የገለታን አስከሬን በደንብ እንዲመለከቱ ከተደረገ በኋላ፣ የገለታን ጭንቅላት ረጅም እንጨት ላይ ሰክተው እንደ ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ እየጨፈሩ ወደ መንደራቸው ተመለሱ።
የገለታና ሻላዬ አሰከሬን የባህላቸውን ስርዓት ተከትለው ሳይቀበሩ የአውሬ ምግብ እንዲሆኑ ተደረገ።

Additional information

Publisher

ማራኪ ቡክስ

Publication Year

2015 ዓ.ም

Reviews

There are no reviews yet.

Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.

Buy Now

0
YOUR CART
  • No products in the cart.