Sale!

አዲስ ጀግና (ባዲገዝና ሌሎችም)

መደብር

Original price was: Br 150.00.Current price is: Br 50.00.

ደሳለኝን የማውቀው ገና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪነት ቆይታችን ነው፡፡ ታታሪነትን ከትህትና ጋር የተሞላ ነው፡፡ በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ እና በልጅነት ዕድሜው ከሚጠበቅበት በላይ በርካታ መጽሐፍትን እያመረተ ለተደራሲ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ መካከል ይህች ‹‹ባዲገዝ›› መጽሐፍ ብዙ ቁም ነገሮችን አካታለች፡፡

በተለይም እንደ ሀገር ያለንበትን ወቅታዊ ስንጥቅ በደንብ የሚፈትሹ፣ የሚያስገነዝቡ፣ ከእንቅልፋችን እንድንነቃ ጆሯችን ላይ የሚያቃጭሉ እና የሚሄሱ ወጎች ተቀምረዋል፡፡ በተለይም ከሀገር በቀል እውቀት ልምዱ የቀሰማቸውን እንቁ የልጅነት ፍልቅልቅ ትውስታዎች ከዛሬው እኛነታችን ጋር እያጋመደ ሀገራዊ ተብሰልስሎትን፣ ማህበራዊ መስተጋብርን፣ ሰውነትን (ኢትዮጵያዊ እሴትን)፣ ኪነ-ጥበብን፣ ማህበረ-ፖለቲካን፣ በትዝብት መንቆር እየነቀሰ ያስኮመኩመናል፡፡

ነግና ሰርክ የሚኮረኩሩን፣ እንደ አልባሌ በጎንዮሽ የምናልፋቸው፣ ውስጥ ውስጡን የሚከነክኑንን ርዕሰ-ነገሮች በማንጠር በንስራዊ እይታው በብዕሩ እየገለበ ድጋሜ እንድናጤናቸው ብሎም እንድንደመምባቸው ጭምር ይጋብዘናል፡፡ ደሳለኝ ከዚህም በላይ ሊገለጥ የሚችል የታመቀ የአምራች ፀሐፊነት አቅም እንዳለው በፅኑ እንዳምን አድርጎኛልና የማይነጥፍ ብዕሩን በ‹‹ባዲገዝ›› ታድሜያለሁ፤ ሌላውን አንባቢ ይመርምር፡፡

ዳኜ አበበ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር መምህር

Description

መኖር ማለት ምንድን ነው ? ሕይወትስ ? ደራሲው “ጥንት አባቶቻችን” ለሚላቸው አንደበታቸው ለሚጠና ፣ ዕውነት ከግንባራቸው ለተጻፈ፣ ሕይወትን በጥበብ ለሚዳስሱ አበው ከልቡ ከትቦ ፣ ከአዕምሮው ያሰረፀው አክብሮትና አኮቴት አጥንትን ሰርስሮ ዘልቆ የሚሰማ ነው።

እግዚአብሔር ለተፈጠረው ሰው ከሴትም ፣ ከጎጆም ፣ በፊት ሥራን ሰጠው። “የዔድን ገነትን ይጠብቅና ያበጅ ዘንድ”። ደሳለኝ ትውልድ የተቀባው የልዕለ ሰብእነት ረቂቅ ፀጋ መገኛው ቢጠፋው ‘የት ነህ’ እያለ ይጠይቃል። “ይህ ትውልድ ዓለም ወደ እርሱ እየቀረበች ፣ እርሱ ከጎረቤት ጋር ለመኖር የሚቸገር ” በማለት ዘመኑ መጥቆ ሔዶ ሲያበቃ ወዲህ ደግሞ የሰው ልጅ ምድር ጠባው ቃየናዊ ቁጣው ገንፍሎ ሲንተከተክ ይንገበገባል። ማኅበራዊ መስተጋብር፣ ታሪክ፣ ፖለታካና ኢኮኖሚ፣ ገጠመኝ፣ የእንጀራ ገመድ የመጽሐፉ ዙሪያ መለስ መሽከርከሪያዎች ናቸው። ሥራዎቹ የሕይወት ጥዋትና ማታ ስንስል ማያ ፣ የንዑድ ሀሳቦች ማጠንጠኛም ሰበዞች ናቸው። ታሪክን ከመውደድ አልፎ ይሳሳለታል። መጽሐፉ የሰውን ልጅ የለመሆን መሻት፣ አይሆኑ መብከንከን ፍንትው አድርጎ ይዳስሳል።

ከንጋት እስከ ንጋት ፣ ከገጠር እስከ ከተማ የሰው ሃሳብ፣ እምነት ተስፋ እና ጭንቀቱ ፣ ኑሮና ብልሃቱን በበር አስገብቶ ጓዳ ዘልቆ ያስቃኛል።
ፍቅር ሰውን ምን ያደርጋል ? በዚህ ብእር መልሱ ይገኛል። ሥርዓተ ማኅበር ሲዝል፣ አቅም አቅቶት ሲልፈሰፈስ ንፁሕ ዓየር ልጨብጥ ባይ ኑባሬን ማስከተሉ አይቀርም። ይሄኔ ደራሲው “ጠማማው ይቃና ዘንድ አይችልም” ቅዱስ ቃልን ተገዳዳሪ ሆኖ ይመጣል። የሕይወት ልምድና ገጠመኞቹን በፈዛዛ አላለፋቸውም። ቅንብብ ፣ ሽክፍ አድርጎ ዳሰሳቸውና ሰው በእዝነ ልቡናው ብቻ ሳይሆን ነገሬ ብሎ ሁነቶቹን በቁም ነገር ይሰበስብ፣ ይሸክፋቸው ዘንድ መስታውት ሆኗል። መኖር ማለት ይህ ነውና።

ጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጨ
የዶቸ ቬለ ሬዲዮ አዲስ አበባ ወኪል

Reviews

There are no reviews yet.

Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.

Buy Now

0
YOUR CART
  • No products in the cart.