Guidelines for Clients and Authors

About

አበባቢ ነዎት? አንባቢ ከሆኑ Authors’ Registration የሚለው ማውጫ ውስጥ መግባትና መመዝገብ አይጠበቅብዎትም።
ለመጀመሪያ ጊዜ ግዢ ሲፈጽሙ የግዢው ሂደት መጨረሻ ላይ ፎርም እንዲሞሉ ይጠየቃሉ።  እንደደንበኛም ይመዘገባሉ። በሌላ ጊዜ ሲመለሱ  እንደገና መመዝገብ ሳይጠበቅብዎ ግዢ መፈፀም ይችላሉ። ዳውንሎድ የሚያደርጉት ኢቡክ የሚደርስዎ ሲመዘገቡ በሚያስገቡት ኢሜል ነው። 
አንባቢ ነዎት? እንባቢ ከሆኑ በዚህ ድረገፅ ላይ አብዛኞቹን ኢትዮጵያዊ ደራሲያን እና ጸሐፍት ሥራዎች ያገኛሉ። ሁሉም ሥራዎች በአራት ዋና ዋና ካታጎሪዎች ተመድበዋል። ከዋናው ማውጫ Books  የሚለውን በመጫን ያገኟቸዋል። በተጨማሪም በየወሩ እና በየሦስት ወሩ የሚወጡ መጽሔቶችም ተካተዋል። መጽሐቶችን በተመለከተ ለማመሳከሪያነት ያገለግሉ ዘንድ ወደኋላ በመመለስ በርካታ እትሞችን ለመጫን ተሞክሯል። 
ግዢ ለመፈፀም መጀመሪያ ከመረጡት መጽሐፍ ሥር ያለውን “ወደዘንቢል ክተት” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። በዚህ መንገድ የሚፈልጓቸውን መጽሐፍት ወደዘንቢል  አስገብተው ሲጨርሱ ፥ ከገጹ በስተቀኝ አናት ላይ የሚገኘውን የዘንቢል ምልክት ይጫኑ። በውስጡ የተመረጡትን መጽሀፍት ይዞ ያገኙታል። ያለፍላጎትዎ የገባ ካለ ካጠገቡ ያለውን የ X ምልክት ተጭነው ከዘንቢልዎ ሊያስወጡት ይችላሉ።
ደንበኛችን ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ ከድረገፃችን እየገዙ ከሆነ ክፍያ ሊፈፅሙ ሲሉ አንዴ ብቻ እንዲመዘገቡ ይጠየቃሉ። ጥያቄዎቹ አጭርና ግልፅ ናቸው። ሌላ ጊዜ በድጋሚ ሲመለሱ የሚያስፈልግዎ ዩዘር ኔም እና ፓስዎርድ ማስታወስ ብቻ ነው። ፓስ ወርድ ከረሱም ችግር የለም እኛ እናግዝዎታለን። 
ከዋናው ማውጫ My Account የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ ከውስጡ Download የሚለውን ያገኛሉ፤ በየጊዜው የገዟቸው መጻሕፍት የማውረጃ ሊንክ ከነፓስዎርዱ ሁል ጊዜም በዚህ ይኖራል። ያወረዱት መጽሐፍ ባጋጣሚ ቢደመሰስብዎ ክምችትዎ በዚህ ይገኛል። 
የመጽሐፍ ህትመት ግብዓት ዋጋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ ከ500% በላይ ጭማሪ አሳይቷል። የህትመት ግብዓት ዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን በሚፈለገው መጠን አለመገኘቱም ሌላ ተጨማሪ ችግር ሆኗል። በዚህ ምክንያት የታተሙ መጽሐፍት ዋጋ እጅግ ከፍ ከማለቱ የተነሳ መጽሐፍ ማሳተም፥ ወይም ገዝቶ ማንበብ ለብዙዎቻችን ቅንጦት ወደመሆን እየተሸጋገረ ነው። 
መጽሐፍ በሀርድ ኮፒ መግዛት ለሚፈልጉ ብቻ (Book on demand/ Print on demand) ሲጠይቁ አትሞ በማቅረብ የዋጋ ውድነቱን እንዲሁም ያልተፈቀደ የመጽሐፍ ማባዛት ሂደትን ማስቀረት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ በሶፍት ኮፒ ገዝተን ማንበብ ባህላችን ብናደርግ ከፍተኛ ቁጥር ላለው አንባቢ ማዳረስ ከመቻሉም በላይ በህትመት ግብአት ግዢ የሚወጣውን የማይናቅ መጠን ያለው የውጪ ምንዛሪ ማዳን፤ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ተጨማሪ የውጪ ምንዛሪ ማስገኘት ይቻላል። 
ከኢትዮጵያውያን ደራሲያን መካከል መጽሐፍ ጽፌ እና ሽጬ ሂይወቴን ባግባቡ መምራት የሚያስችለኝን ገቢ ማግኘት ችያለሁ የሚል ፈልጎ ማግኘት ከባድ ነው። የሚታተሙ መጽሐፍት ቁጥር ከአጠቃላይ ከተማረውና ማንበብ ከሚችለው ዜጋ ቁጥር ጋር ሲነፃፀሩ 1% እንኳን አለመሆናቸው፤ ስርጭታቸውም ቢሆን በመሀል ሀገር እና ጥቂት በሚባሉ ከተሞች መወሰኑ፤ ይሄም ቢሆን ተሸጦ ባግባቡ ደራሲው ኪስ የማይገባ መሆኑ በግልፅ ይታያል። የኛ አላማ አንድ ስኒ ቡና በማይገዛ ዋጋ መጽሀፍን ለዜጉች ማዳርስ እና ከብዛት ደራሲያን ጠቀም ያለ ገቢ አግኝተው የበለጠ ለመሥራትና በሙያቸው ህዝብ ለማገልገል እንዲበረታቱ ማድረግ ነው።
ለዚህ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ለሚያደርግ ዓላማ ታማኝ መሆን ጥቅሙ ሁለንተናዊ ነው፤ ሀገር፥ ህዝብ፥ ባጠቃላይ ትውልድ ይጠቀማል። በጣም አነስተኛ በሆነ ዋጋ የገዙትን ሶፍት ኮፒ ለራስዎ ብቻ በመያዝ እና ሌሎች እንዲገዙ በማበረታታት ቅንነትዎን ያስመስክሩ።
በተቻለ መጠን በድረገጻችን፥ በሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተፃፉ መጻሕፍት እንዲካተቱ ጥረት ይደረጋል። ከተከታይ ቁጥር አንፃር ዋና ዋና የሚባሉትን ሀይማኖቶች መሠረት አድርገው የተጻፉትም ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል። በኢትዮጵያውያን ጸሐፍት፥ በውጪ ቋንቋዎች የተዘጋጁትም ቢሆኑ ቦታ አይነፈጋቸውም። የልብዎን ጠንቅቀን ባናውቅም የፍላጎትዎን ለመሙላት ግን  እንጥራለን። 
እውቀትን ከሀገር እስከ አገር፥ ከአፅናፍ እስከአፅናፍ በማደላችን፥ በጠፋና በተወደደ የህትመት ግብዓት ግዢ ምክንያት የሚባክነውን የውጪ ምንዛሪ በማዳናችን፥ አልፎም በመላው ዓለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደንብኞቻችን የውጪ ምንዛሪ በማምጣታችን፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በጉስቁልና ውስጥ እንኳን ሆነው እኛን ለማገልገል ሌትና ቀን የሚባትሉትን እውቀት ቀማሪዎች የድካማቸውን እንዲያገኙ በመሥራታችን ኩራት ይሰማናል።  አማዞን ከኛ ተቀብሎ ለሌላ የሚሰጥ እኛ ከኛው ለኛው ሁሉንም የምናካፍል ኢትዮጵያዊ አባይ እንደምንሆን በፅኑ እናምናለን። 
ደራሲ ወይም ተርጓሚ ከሆኑ Authors’ Registration የሚለውን ማውጫ ተጭነው ምዝገባዎትን ይጀምሩ። መጠይቆቹ እንድ ጊዜ ብቻ የሚሞሉ ቢሆኑም በርከት ስለሚሉ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማጠናቀቅ አይጠበቅብዎትም፤ 
ለጊዜው መረጃዎቹን አሟልተው ባይመዘገቡም ወደፊት መደብርዎን ከከፈቱ በኋላ ቀስ በቀስ አንድ መደር በሚፈልገው ነገር ማሟላት ይችላሉ። መደብር ከውጪ ደንበኞቹን የሚጠራበት አርማ፥ ባነር የመሳሰሉ ገፅታን አሳማሪ ነገሮች ያስፈልጉታል።
አንድ የመጽሐፍ መደብር የከፈተ ደራሲ መጽሐፎቹን ባግባቡ መደርደር እንደሚያስፍልገው ሁሉ እርስዎችም የመጽሐፎቹን የፊት ለፊት ገጽ፥ ስፓይን እና የጀርባ ሽፋን ቀድመው ቢያዘጋጁ ይመረጣል። 
በማራኪ የኢቡክ ገበያ ውስጥ የርስዎ መደብር መሉ ለሙሉ የግልዎ ነው። በወደዱት መንገድ የሚያድራጁት እና የሚያስውቡት ከሁሉም በላይ ደግሞ ከእርስዎ በስተቀር ማንም የማይገባበት፥ እያንዳንዱን መረጃ የሚከታተሉበት ገንዘብዎን ቀንና ሰዓት እየጠበቀ ደቂቃ ሳያዛንፍ በባንክዎ የሚያደርግልዎ የማይዋሽ፥ የማያታልል፥ ጓዳ ተደብቆ የለም የማያሰኝ፥ ነገ ተመለስ የማይል፥ እባክህ የማይሉት የደረጅ ሥርዓት ነው።
ከደንበኞችዎ ጋር በቀጥታ ያለሌላ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ይወያያሉ፥ መረጃ ይለዋወጣሉ፤ ጥያቄ ይመልሳሉ፥ ፍላጎቱ ላላቸውም ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ታዲያ ምን ይላሉ?

News & Events

መጽሐፍን ሳያሳትሙ ያስመርቁ!!

መጽሐፍን ሳያሳትሙ ያስመርቁ!! ውድ የማራኪ ቡክስ ቤተሰቦች፥ የመፅሐፍ ህትመት ዋጋ ከጊዜ ጊዜ መናር ደራሲያንን እና የመፅሐፍ ስርጭቱን በጣም እየፈተነ መሆኑ ለሁላችንም ግልፅ ነው። ማራኪ ቡክስ

Read More »

ማራኪ ቡክስ

ውድ ደራሲያን እና አንባቢያን ከማራኪ ቡክስ ጋር ስለሆናችሁ በጣም እናመሰግናለን። ማራኪ ቡክስ ከመፃፍ፥ ከማንበብ፥ ከመሸጥ እና ከመግዛት በላይ በመጽሐፍ ውስጥ ሌላ ግብ አለ ትላለች። ይህ

Read More »

ምስጋና

በቅርቡ በርካታ ታዋቂና ድንቅ ደራሲያን ማራኪ ቡክስን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። በግልም በቡድንም ስናነጋግራችሁ አብራችሁን ለመሥራትና ደራሲያንን ተጠቃሚ የማያደርገው ባህላዊው የመጽሐፍ ስርጭት ሥርዓት እንዲሻሻል፤ የገበያውን አድማስ በማስፋት

Read More »

ማራኪ ቡክስ የኢትዮጵያን የመጽሐፍ ስርጭትና ንግድ ሥራ አዲስ ገጽታ የሚያላብስ  አሠራር ጀመረ

በኢትዮጵያ ውስጥ ደራሲ ወይም ተርጓሚ ሆኖ መጽሐፍ መጻፍ አበረታች አይደለም፤ በተለይም  ከህትመቱ ጀምሮ እስከስርጭቱ ያለው አጠቃላይ ሂደት ብዙዎች ሊያስቡት እንኳን የማይፈልጉት አታካች ጉዳይ እንደሆነ ተደጋግሞ

Read More »

Help Post

ደራሲ ወይም ጸሐፊ ከሆኑ ለመመዝገብ ከዋናው ማውጫ ላይ Authors’ Registration የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። በገፁ ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች ባግባቡ ከመለሱ በኋላ የመጨረሻውን ቁልፍ ሲጫኑ መደብርዎን በማደራጀት ሂደት

Read More »

ያልተደረሰበት ከፍታ

ሙሉ አቅምን ለመግለጥ የሚረዱ ያልተለመዱ ጥበቦች ኢ-ቡክ ለሁሉ አዲስ አድማጮች በነፃ የተበረከተ ኩፖን ኮድ hulu ID: 5096

Read More »
0
YOUR CART
  • No products in the cart.