ደራሲ ወይም ጸሐፊ ከሆኑ ለመመዝገብ ከዋናው ማውጫ ላይ Authors’ Registration የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። በገፁ ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች ባግባቡ ከመለሱ በኋላ የመጨረሻውን ቁልፍ ሲጫኑ መደብርዎን በማደራጀት ሂደት የሚያግዝዎ ገጽ ይመጣል። በአያንዳንዱ ደረጃ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ሲያስገቡ ወደሚቀጥለው እያሻገረ  እስከፍፃሜው ይከተልዎታል።  ሂደቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚከናወን ስለሆነ በጥንቃቄ ቢያደርጉት ይመረጣል። ትክክለኛ መርጃዎችን ብቻ በማስገባት ሂደቱን የማያዳግም ያድርጉት። በተለይ የባንክ መረጃዎችዎን በጥንቃቄ ያስገቡ፤ የተሳሳተ መረጃ ካስገቡ ገንዘብዎ ወዳልተፈለገ አድራሻ ሊሄድ እንደሚችል አይዘንጉ። ከዚህ በኋላ የግልዎ የሆነው የመጽሐፍ መደብር ተከፈተ ማለትነው።

የግል መደብርዎን መክፈትና መቆጣጠር የሚችሉት  በገፁ አናት  ላይ ከሚገኘው ዋናው ማውጫ ላይ Author’s Book Shop የሚለውን ሲጫኑ ነው። ወደዋናው ሞል አልገቡ ከሆነ ዩዘር ኔም እና ፓስወርድ እንዲያስገቡ ይጠየቃሉ። ገብተው ከሆነ ግን በቀጥታ የራስዎ መደብር ውስጥ ያለምንም ቁልፍ ጥልቅ ማለት ይችላሉ።  በመደብርዎ ውስጥ የሚሸጧቸውን መጽሐፍት ብዛት ዓይነትና ዋጋ የሚወስኑት እርስዎ ብቻ ነዎት። ከደንበኞችዎ ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ። የደንበኞችዎን ፍላጎት ያዳምጣሉ፤ አስፈላጊውን ምላሽና ድጋፍ ያደርጋሉ። በየደቂቃው በእጅ ስልክዎ ላይ ማን እንደገዛዎት፥ ምን ያህል  እንደሸጡና ምን ያህል ኮሚሽን እንደከፈሉ ያያሉ፥ ይቆጣጠራሉ። መደብር የሌላቸውን ወይም ለመክፈትና ለመቆጣጠር የማይፈልጉ ወይም በተለያየ ምክንያት የማይችሉ ደራሲ ወዳጆችዎን መጽሐፍት በመደብርዎ እየሸጡ ጥቅም መጋራት ይችላሉ። ምንም የማያሻማ የማያጠራጥር አሰራር ስለሆነ ከወዳጅዎ ጋር አይቀያየሙም። 

በማራኪ ቡክስ ላይ የሚሸጡ መጻሕፍት በዚያው በድረገፁ ላይ የሚነበቡ ወይም ወርደው ደንበኛው ባለው ወይም በሚመርጠው መሣሪያ ላይ የሚነበቡ ናቸው።  እዚህ ጋ መጽሐፎቹ  ወርደው የሚነበቡ ከሆነ አላግባብ ለመባዛት እና ለስርቆት አይዳረጉም ወይ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። 

ለዚህ ችግር በሚገባ ታስቦበታል፤  ማንኛውም ኢቡክ ለመታተም፥ በክፊልም ሆነ በሙሉ ኮፒ ለመደረግ፥ ወይም ኤዲት ለመደረግ አይችልም። ሙሉ ለሙሉ የተቆለፈ ከመሆኑ ባሻገር በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የገዢው ኢሜልና ሌሎች መረጃዎች በፅሁፍና በባር ኮድ ንባብን በማይከለክል መልኩ በስሱ ተደጋግመው ይታተሙበታል (ወተር ማርክ ማለት ነው) በዚህ ሁኔታ የግል መረጃው ያለበትን ሶፍት ኮፒ ለሌሎች አሳልፎ የሚሰጥ ደንበኛ እንደማይኖር ይታመናል። 

መጽሐፍ እንዴት ልጫን?

መጽሐፎችዎን በመጀመሪያ በpdf ወይም  epub ፎርማት ያዘጋጁ።  በመቀጠል ከማውጫው ላይ Book Stores የሚለውን በመጫን ሙሉ መደብርዎትን መቆጣጠር መጻሕፍትን መጫን የባንክ አካውንትን ጨምሮ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ማ ስገባት ይችላሉ። 

0
YOUR CART
  • No products in the cart.