ያልተደረሰበት ከፍታ

ያልተደረሰበት ከፍታ Nebiyu Tefera

 • በመጠኑም ቢሆን ደስ የሚል ሕይወት እንደኖርኩ ለማመን የመጀመሪያ

  መሆን አለብኝ። ከሌላው በተለየ ምቹ ሁኔታ ውስጥ ህይወትን

  አልጀመርኩም፤ ምናልባትም ከአንዱ በስተቀር—ወደ ከዋክብቱ

  እንድደርስ ያበረታቱኝ ድንቆቹ ወላጆቼ። በሚያስደንቅ የጉዞ ምዕራፍ

  ህይወትን ያስጀመረኝን ቀላል እና ዘላቂ ጥበብ ሰጡኝ።

  የፖስታ ማምረቻ ኩባንያዬን መገንባቴ፥ የኒው ዮርክ ታይምስ ቁጥር አንድ

  ደራሲ እና አነቃቂ ተናጋሪ መሆኔ እንዲሁም አንዳንድ አስገራሚ

  ዝግጅቶችን እና ፕሮጀክቶችን ለመምራት በጎ ፈቃደኛ መሆኔ፥ ገንዘብ

  የማይገዛቸውን ልምዶች አስገኝቶልኛል። ከአምስት አሥርት ዓመታት

  በላይ የዘለቀው የንግድ ሥራዬ አሁንም ብዙ መማር እንዳለብኝ

  አስገንዝቦኛል፤ ቤተሰቦቼ፥ ጓደኞቼ እና አማካሪዎቼ ባለፉት ዓመታት

  ላካፈሉኝም ጥበብ አመሰግናለሁ።

  መጽሐፎቼ ሰባቱ የኒው ዮርክ ታይምስ ምርጥ ሽያጭ ውስጥ የገቡ ሲሆን

  ከነዚያ መካከል ሦስቱ አንደኛ ደረጃን ያገኙ ናቸው፤ እና በሀገር አቀፍ

  ደረጃ በሚታተሙ አምዶቼ አማካይነት ምክሮችን አጋራሁ፤ እንዲሁም

  አጫጭር መረጃዎችን አካፈልኩ። ብዙውን ጊዜ ሥራ የሚበዛባቸው

  አንባቢዎች በመልእክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑና እንደየሁኔታው

  በሥራቸው ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ተስፋ በማድረግ በአንድ

  ጊዜ በአንድ ነጠላ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ብቻ አተኩራለሁ።

  ነገር ግን ይህ መጽሐፍ፤ ሕይወቴን ሙሉ፥ ከወላጆቼ ተረክበው

  አብረውኝ ከኖሩት ሰዎች ጋር በምሠራበት ጊዜ ሁሉ የቀሰምኳቸውን

  ምርጥ ትምህርቶች አጠናቅሮ የያዘ በመሆኑ በእውነት ትልቁና ዋናው

  ነው። ታሪክ የመንገር ፍቅሬ፥ ለዘመናት የአሶሺዬትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ

  የነበረው የአባቴ ስጦታ ነው፤ እንዲሁም የዕድሜ ልክ የመማር ፍቅርን

  በውስጤ ያስቀመጠች ደግሞ አስተማሪ እናቴ ናት። ቤተሰብ፥

  ጓደኞች፥ የንግድ ሥራ ተባባሪዎች እና ተወዳዳሪዎች፥ የማኅበረሰብ

  መሪዎች እና ተዘርዝረው የማያልቁ አዋቂዎች ምናቤን ያሰፉ ዕድሎችን

  ሰጡኝ። የተማርኩትን፥ የሠራሁትን፥ ያልሠራሁትን፥ የምለውጠውን

  እና የማመሰግንበትን ነገር ሁሉ እንዳካፍል አበረታቱኝ።

  ወደዚህ መጽሐፍ የመጣውም ይኸው ነው። እርስዎ በሚቀጥሉት ገጾች

  ውስጥ መነቃቃት እንደሚያገኙ እና የተሻለውን ሕይወትዎን እንደሚኖሩ

  ተስፋ አደርጋለሁ።

  ለእርስዎ የማስተላልፈው መልእክት፥ በመጀመሪያ ውድቀትን ከሁሉም

  በላይ ደግሞ ስኬትን አይፍሩ።

  ሃረቬይ ማኬይ (ደራሲ)

 • Maraki Books
 • June 24, 2024

Similar Posts

0
YOUR CART
 • No products in the cart.