መጽሐፍና መጽሔት በድረገጽና በሞባይል መተግበሪያ የማከፋፈልና የመሸጥ ስምምነት ውል፤

ውል ሰጪ፦ ባለ’ጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ (ማራኪ ቡክስ) አድራሻ፡- አ/አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 217/A ስልክ ቁጥር 0911602370 ከዚህ በኋላ ውል ሰጪ ተብሎ ይጠራል፡፡ 
ውል ተቀባይ፦  ማንኛውንም የራሱን የፈጠራ ሥራ ወይም የሌላ ሰው የፈጠራ ሥራ የሆነውን ተርጉሞ መጽሐፍ ያዘጋጀ፤ ያዘጋጀውን መጽሐፍ የታተመውን ወይም የማይዳሰሰውን ቅጂ፥ ወይም በመጽሐፍ መልክ እንዲታተምለት ጭምር ተስማምቶ የሥራውን ውጤት ለውል ሰጪ ያቀረበ አካል ወይም በማራኪ ቡክስ ድረገፅ ላይ ሥምና አድራሻውን ሞልቶ፥ ይህን ውል አንብቦና ተስማምቶ የመጽሐፉን የማይዳሰስ ቅጂ የጫነ ግለሰብ፥ ድርጅት፥ ማህበር ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ ተብሎ ይጠራል። የዚህ ውል የኤሌክትሮኒክ ቅጂ በማራኪ ቡክስ የመጽሐፍ መሸጫ ሥርዓት ላይ ተጭኖ ውል ተቀባዩ መስማማቱን ካረጋገጠበት እና በራሱ ፈቃድ በደራሲነት ተመዝግቦ የፈጠራ ሥራው ወይም የፈጠራ ሥራዎቹ በድረገጹ ላይ እንዲሸጡለት ሲያስገባ ይህን ውል አንብቦና ተረድቶ እንደተስማማ እና እንደፈረመ ይቆጠራል። ደራሲው ወይም ተርጓሚው በሀገር ውስጥ የሚኖር ሲሆንና በአካል ተገኝቶ ለመፈራረም አመቺ ሁኔታ ሲኖር ውሉ በወረቀት ተዘጋጅቶ በአማራጭነት እንዲፈረም ይደረጋል። 
አንቀፅ አንድ፦ ትርጓሜ 
1.1 ደንበኛ፦ ከማራኪ ቡክስ ድረገጽ ላይ መጽሐፍ መርጦ፥ በኦንላይን ዘዴ ከፍሎ በመግዛት የሚያነብ ወይም የሚያዳምጥ ግለሰብ በዚህ ውል ላይ ደንበኛ ተብሎ ይጠራል። 
1.2. ደራሲ፦ www.marakibooks.com ድረገፅ ላይ መጽሐፉ እንዲሸጥለት ተስማምቶ ያቀረበ ደራሲ፥ አዘጋጅ፥ ተርጓሚ ወይም አሳታሚ መጽሐፉን የማባዛት እና በማንኛውም መልኩ የመሸጥ ህጋዊ የውክልና ስልጣን የተሰጠው ግለሰብ ወይም ሌላ የህግ ሰውነት ያለው አካል በጥቅሉ ደራሲ ተብሎ ይጠራል። 
1.3. ማራኪ ቡክስ ኦንላይን የኢቡክ ገበያ፦ www.marakibooks.com በሚል የድረገጽ አድራሻ የሚገኝ ሲሆን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የመጽሐፍ ቅጂዎችን በመላው ዓለም ላሉ ደንበኞች እያቀረበ ለመሸጥ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ ህጋዊ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ከደራሲያን፥ ተርጓሚያን፥ አዘጋጆችና አሳታሚዎች የተቀበላቸውን መጻሕፍት በገጹ ላይ በማውጣት፥ በማስተዋወቅ እና ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግ ውል ተቀባዮች ቆርጠው ከሰጡት ዋጋ ላይ ከ20 እስከ 30 ፐርሰንት ኮሚሽን በመቀነስ ገቢ የሚያገኝ ተቋም ነው። ሥራውን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ከሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የዴሊቨሪ ኩባንያዎች ከፋይናንስ ተቋማት እና ኦንላይን የሽያጭ ሥርዓት ከሚያለሙ ድርጅቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይሠራል። 
1.4. ሲፈለግ ብቻ የሚታተም መጽሐፍ (Book ON Demand)ማለት ቀድሞ በብዛት በወረቀት የታተመ መጽሐፍ ሳይኖር ደንበኛው የግዢ ጥያቄ ሲያቀርብ ወዲያውኑ ታትሞ የሚቀርብ መጽሐፍ ማለት ነው። በዚህ ውል መሠተት ሂደቱ ኦን ዲማንድ ፕሪንቲንግ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ ማተም ተብሎ ይጠቀሳል። ለውል ተቀባዩ ወይም ለደራሲው በርካታ ጠቀሜታዎች ሲኖሩት ዋና ዋናዎቹ፥ አስቀድሞ ብዙ ሺህ ኮፒ ለማተም የሚያስፈልገውን ወጪ ስለሚያስቀር የማሳተሚያ ገንዘብ እጥረት ውስጥ የገቡ ደራሲያን ያለችግር ሥራዎቻቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ ያግዛል። የታተመው መጽሐፍ በተጠበቀው ጊዜ ባይሸጥ የሚያስከትለውን ኪሣራ ይቀንሳል በብዛት ታትሞ በገበያ ላይ የሚሰራጭ ባለመሆኑ መጽሐፉ ተመሳስሎ ታትሞ ለገበያ ሲቀርብ ለመከታተል እና በሕግ ለመጠየቅ ይረዳል። መጽሐፉ ሲፈለግ ብቻ ታትሞ እንዲቀርብለት የተስማማ ድራሲ/ ተርጓሚ / አዘጋጅ/ አሳታሚ በሌላ መንገድ አሳትሞ ለገበያ አቅርቦ ተመሳስሎ ቢታተምበት ኃላፊነቱን ራሱ ውል ተቀባይ ይወስዳል። 
1.5. የማይዳሰስ ቅጂ፦ ማለት አንድ መጽሐፍ በወረቀት ላይ ከመታተሙ በፊት በተለያየ የፋይል ፎርማት በኮምፒዩተር፥ ታብሌት ወይም የስልክ ቀፎ ላይ በሚከማችበት ሁኔታ እንዳለ ለአገልግሎት ሲውል ማለት ነው። በዚህ ውል ውስጥ የማይዳሰስ ቅጂ በጆሮ የሚደመጥ ሲሆን ኦዲዮ ቡክ ወይም በአይን እየታየ የሚነበብ ሲሆን ኢቡክ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። 
1.6. ኦዲዮ ቡክ፦ የደራሲው/ የተርጓሚው/ ያዘጋጁ ሥራ በአርቲስቶችና በጋዜጠኞች ተተርኮ በጆሮ የሚደመጥ መጽሐፍ (Audible) ሆኖ ይዘጋጃል፤ ከቀረፃ እስከ አርትኦት የሚያስፈልጉ ወጪዎች የሚሸፈኑት በውል ሰጪ ነው። ደንበኛው በድረገፅ እና በሞባይል መተግበሪያ ክፍያ ፈፅሞና ወደመጠቀሚያ መሣሪያው አውርዶ ማዳመጥ ይችላል። በሀገራችን የጠቅላላውን ህዝብ 10% የሚሸፍኑት ማየት የተሳናቸውን እና ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ለማንበብ ጊዜ የማይኖራቸውን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ ለመጽሐፍ ንግድ አዲስ ገበያ ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል። 
 
1.7. ማራኪ ቡክስ ሞባይል መተግበሪያ፦ የማራኪ ቡክስ ድረገፅ ተቀፅላ ሲሆን ከፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር ላይ በነፃ በማውረድ መጠቀም ይቻላል። ሞባይል መተግበሪያው ኦዲዮ ቡክ እና ኢቡክ ለመሸጥ የሚያስችል ነው። ደራሲው/ተርጓሚው/አዘጋጁ መጽሐፉ በኢቡክ እና በኦዲዮ ቡክ መልክ እንዲሸጥለት ሲስማማ አመቺ በሆነ ፎርማት ተዘጋጅቶ ይጫናል። ውል ተቀባይ ሙሉ መረጃውን አስገብቶ ተመዝግቦና ከውል ሰጪ በኩል ወደመተግበሪያው የመግባት ፈቃድ ካገኘ በኋላ የራሱ መጽሐፍ ምን ያህል እንደተሸጠ፥ ማን እንደገዛው፥ ምን ያህል ገንዘብ እንዳለው እና ምን ያህል ኮሚሽን እንደከፈለ የመከፍታተል ዕድል ይሰጠዋል። 
አንቀፅ ሁለትየውሉ ዓላማ ውል ተቀባይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከአዕምሮው አመንጭቶ ወይም የሌላ ደራሲን ሥራ ተርጉሞ ያዘጋጀውን መፅሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ከዚህ በፊት ለገበያ ቀርቦ የነበረውን በድጋሚ ለአንባቢያን በማራኪ ቡክስ አማካኝነት እንዲሸጥለት በመፈለጉ የተፈፀመ ውል ሲሆን ውል ሰጪም የውል ተቀባዩን ሥራ በመጽሐፍ መልክ የታተመውን ወይም የማይዳሰስ ቅጂውን ተቀብሎ ለአንባቢያን ለማዳረስ ውል ተቀባይ የቆረጠውን ዋጋ በተሸጠው የመጽሐፍ ብዛት እያሰላ እና ኮሚሽኑን እየቀነሰ ከእጅ ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ በቀጥታ በደራሲው አካውንት ገቢ እንዲያደርግ ውል ተቀባይ እና ውል ሰጪ መካከል የተፈፀመ ውል ነው። 
ይህ ውል በኢትዮጵያ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ አናርኛ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። እንዳስፈላጊነቱ በሌሎች ብሔር ብሄረሰቦች ቋንቋ ተዘጋጅቶ ሊቀርብ ይችላል።
 
አንቀፅ ሦስት፦ ኃላፊነቶች እና ግዴታዎች 
 
የውል ሰጪ ግዴታዎች ውል ሰጪ ከውል ተቀባይ ለመሸጥ የተረከበውን መጽሐፍ በደረገጽ አማካኝነት ለገበያ በማቅረብ ይሸጣል። ክፍያውንም በተሸጠው መጽሐፍ ልክ በማራኪ ቡክስ የመጽሐፍ መሸጫ ሥርዓት አጋዥነት እያሰላና እያሳወቀ ይከፍላል። ደራሲው/ተርጓሚው አዘጋጁ ውል እንዲቋረጥ ሲፈልግ በቀጥታ ወደሥርዓቱ በመግባት መጽሐፎቹን ከድረግፁ ላይ ማንሳት ይችላል። ውል ተቀባይ መጽሐፉ ሲፈለግ ብቻ እንዲታተምለት እና በወረቀት ቅጂ እና በኤኬክትሮኒክስ ቅጂ እንዲሸጥለት ለውል ሰጪ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሰጠ እንደሆነ የማይዳሰስ ቅጂው ለህትመት በሚሆን መልኩ ለሌላ ሦስተኛ ወገን እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል። የመጽሐፉ የገበያ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረ እና ውል ሰጪ የውል ተቀባይን ተጨማሪ የጽሑፍ ስምምነት ካገኘ አስቀድሞ በብዛት ሊያትም ወይም እንዲታተም ሊያደርግና ሊያሰራጭ ይችላል። ድረገጹን እና የሞባይል መተግበሪያውን በየጊዜው እያዘመነ ሳቢና ላጠቃቀም ቀላል የማድረግ ኃላፊነት አለበት። 
 
የውል ተቀባይ ግዴታዎች በዚህ ውል የተጠቀሰው መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል የቅጂ መብት ወይም የይገባኛል ጥያቄ ቢቀርብበት ምላሽ የመስጠቱ ሙሉ ኃላፊነት የውል ተቀባይ ይሆናል። በመጽሐፉ ውስጥ ለተካተቱ ይዘቶች መሉ ለሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስደው ውል ተቀባይ ነው። የዘር፥ የፖለቲካ፥ የሐይማኖት እና ሌሎች ልዩነቶችን አጉልቶ በመጻፍ አለመግባባትና ግጭት የሚቀሰቅስ ይዘቶችን እንዲሁም የፆታ እና የቀለም እኩልነት፥ የመንግሥት ህጎችና ደንቦችን እንዲሁም የማህበረሰቡን የሞራልና የሥነምግባር መርሆዎች የሚፃረር ይዘት ያለው መጽሐፍ በማራኪ ቡክስ ላይ መሸጥ አይቻልም። በመሰል ይዘቶች ምክንያት ለግጭት እና አለመግባባት ምክንያት የሆነ ወይም ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የተገመተ ሥራ ባለቤት፥ ሆን ብሎ ሥራውን በማራኪ ቡክስ ላይ የጫነ እንደሆነ ሌሎች ሥራዎቹም በማራኪ ቡክስ ላይ እንዳይሸጡ ሊታገድ ይችላል። ተዋዋይ ወገኖች ከሚያገኙት ገቢ ላይ የመንግሥት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን በየግላቸው ይወጣሉ ። በልዩ ሁኔታ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ድረገፁን የማስተዋወቅ ሥራ የውል ሰጪ ሲሆን፥ በዚህ ውል ላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ/ መጽሐፎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የማስተዋወቅ ኃላፊነት ደግሞ የውል ተቀባይ ነው። 
 
 

አንቀፅ አራት፦ የዋጋ ተመን

ውል ሰጪ የማይዳሰሱ ቅጂዎችን ዋጋ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ጣሪያ የደንበኞቹን አቅምና ፍላጎት አመዛዝኖ ሊተምን ይችላል። ውል ተቀባይ በዝቀትኛው ወለል እና በከፍተኛው የተመን ጣሪያ መሀል ያዋጣኛል የሚለውን ዋጋ ሊተምን ይችላል። ውል ሰጪ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የዋጋ ተመኖች በቅድሚያ መወሰኑ ያለውን ጥቅምና ጉዳት ለውል ተቀባይ የማስረዳት ኃላፊነቱን ይወጣል። አንድ መጽሐፍ በማራኪ ቡክስ ድረገፅ ወይም ሞባይል መተግበሪያ ላይ በኦዲዮ ቡክ፥ በኢቡክ ወይም ታትሞ እንዲሸጥ የመወሰን ስልጣን የደራሲው ወይም የውል ተቀባዩ ነው። ከዚህ ውጪ ውል ሰጪ መጽሐፉን የውል ተቀባዩን ፈቃድ ሳያገኝ በራሱ ፈቃድ በአንዱ ወይም በሌላው መልክ ለሽያጭ ያቀረበ እንደሆነ በጥፋተኝነት ይጠየቃል። ይህን ውል የሚዋዋለው ወገን መጽሐፉን እንዲሸጥ ስልጣን የተሰጠው ሶስተኛ ወገን ከሆነ በዋናው ባለመብት ወይም የመወከል ስልጣን በተሰጠው ሌላ ወኪል የተሰጠውን ህጋዊ ውክልና እንዲያያይዝ ይጠየቃል። ውል ተቀባዩ በማራኪ ቡክስ ድረገፅ ወይም መተግበሪያ ላይ በሚገኙ ምርትን ወይም አገልግሎትን ለማስገባት በተዘጋጁ ቅፆች ላይ የመጽሐፉን/ የመጽሐፎቹን ርዕስ፥ በንም መልኩ እንዲሸጥለት እንደሚፈልግ እና የሚወስነውን ዋጋ በብር እና በዶላር በማስገባት ውሳኔውን ያሳውቃል። ውል ተቀባይ መጽሐፍ/መጽሐፎች/ በማራኪ ቡክስ በኩል ለሽያጭ ቀርበው ከሚያገኘው ጥቅም ላይ ለውል ተቀባይ 30% ለመክፈል ወይም ውል ተቀባይ ከእያንዳንዱ ሽያጭ ላይ ቆርጦ እንዲያስቀር ተስማምቷል። 
 

አንቀፅ አምስት፦ የአከፋፈል ሁኔታ 

 
5.1 ወል ሰጪ  መጽሐፍ ከሚጭኑ ደራሲያን ላይ 30 (ሰላሳ) ፐርሰንት ኮሚሽን ቆርጦ ያስቀራል። ቀደም ብሎ ከደራሲው ወይም ከህጋዊ ባለመብቱ ፈቃድ በማግኘት የተተረኩ ወይም በኦዲዮ ቡክ መልክ የተዘጋጁ መጻሕፍት ሲቀርቡ 15 % (አስራ አምስት ፐርሰንት) ኮሚሽን ብቻ ለራሱ በማስቀረት ቀሪውን ለተራኪዎቹ ወይም ላዘጋጆቹ ይከፍላል፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለደራሲው ወይም ለህጋዊ ባልመብቱ የመክፈል ኃላፊነት የተራኪዎቹ ወይም ያዘጋጆቹ ይሆናል። 
 
5.2 ደራሲያን መጽሐፎቻቸውን ማራኪ ቡክስ ላይ ከጫኑ ወይም እንዲጫንላቸው ከተስማሙ በኋላ የተሳካ ሽያጭ ሲከናወን በማንኛውም ጊዜ  የግላቸው በሆነው ገፅ ላይ ግብይቱን መከታተል እና ከ1 (አንድ) ብር ጀምሮ ወጪ በማድረግ መርጠው ወዳሳወቁት  የባንክ አካውንት ማስተላለፍ ይችላሉ። 
 
5.3 ውል ተቀባይ ክፍያው በደራሲነት ሲመዘገብ በሚሞላው የክፍያ የመረጃ ቅፅ ላይ በሚሞላው  የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ እንዲደረግለት ተስማምቷል/ስች።
 

አንቀጽ ስድስት፦ ውል ስለማቋረጥ

ይህ ውል የሚቋረጠው ውል ሰጪ ወይም ውል ተቀባይ በማንኛውም ምክንያት አንዱ የሌላውን ምዝገባ አቋርጦ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ በድረገጹ ወይም በሞባይል መተግበሪያው ላይ መታየት ሲያቆም ውሉ እንደተቋረጠ ይቆጠራል። ውል ተቀባይም ሆነ ውል ሰጪ ሥራዎቹን ከደረ ገፁ ላይ ቢያነሱ ያነሱበትን ምክንያት የማብራራት ኃላፊነት የለባቸውም። በመጽሐፉ ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል የቅጂ መብት ጥያቄ ሲቀርብ፤ ይዘቱ በሀገርና ሕዝብ ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ላይ አፍራሽ ተፅዕኖ እንዳለው ሲታመን በአስቸኳይ ሽያጩ እንዲቋረጥ በማድረግ ውሉ ሙሉ ለሙሉ ሊቋረጥ ወይም ለጊዜው ሊታገድ ይችላል። የውሉ መቋረጥ የመጨረሻ ውጤት ውሉ ከመቋረጡ በፊት የተከናወኑ ሽያጮች ላይ የተገኘውን ጥቅም ባግባቡ አስልቶ መክፈል ብቻ ነው። የውሉ መቋረጥ በራሱ በተዋዋይ ወገኖች ላይ ምንም ዓይነት የተጠያቂነት ውጤት አያስከትልም። ከክፍያና ከሌሎች መብቶች ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያለው ወገን በመጀመሪያ በውይይት እና በሽምግልና ተሞክሮ ችግሩ መፈታት ያልቻለ እንደሆነ ተበዳይ አግባብ ባለው የሀገሪቱ በህግ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 
0
YOUR CART
  • No products in the cart.