ስለኛ

ባለ’ጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ የተልያዩ አዝናኝና አስተማሪ የሚዲያ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በቴሌቪዥንና ራዲዮ ለማቅረብ እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር 2008 እጋማሽ ላይ የተመሠረተ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ራሱን ባለጅ ብሎ ሲጠራ ዝም ብሎ ባጋጣሚ አልነበረም፤ ይልቁንም የኢትዮጵያ የቀደመ ታላቅነት፥ ስልጣኔ፥ ባህልና ወግ ሲወሳ፥ ታሪካዊ ቅርሶቿ ሲነሱ አብረው በክብር መነሳት የነበረባቸው ባለጆች እስከዛሬ ድረስ የሚሰደቡባት፥ የሚዋረዱባት፥ የሚደበደቡባትና የሚገደሉባት ሀገር መሆኗ በፈጠረው ቁጭት የሥራ ፈርጥ የሆኑ ሙያተኞችን ለማክበር፤ ዛሬም በዘመናዊው ዓለም በእውቀትና በሥነምግባር ሠርተው፥ ለሀገራቸውና ለአካባቢያቸው ጭምር ተጠንቀቀው፥ ህግና ሥርዓት አክብረው ለመበልፀግ የሚሹ በሌቦችና በአጭበረባሪዎች ተውጠው ሌብነት የነገሰበትን ንፅህና ለኪሳራ የሚዳርግበትን አሰራር ለማውገዝ፤ ሥራና ሠራተኞችን ለማክበር የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት
ነው።

ባለጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ ከተመሠረተ ጀምሮ ይህንኑ ሀሳብ የሚያንፀባርቁ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን እና የራዲዮ መሰናዶዎችን በማቅረብ ዘልቋል። በሂደቱም የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ለማሳየት ከመጣር ባሻገር በእውቀትና በሥነምግባር ሠርተው መበልፀግ የሚሹትን ሁሉ በመረጃና በእውቀት አቅርቦት በመደገፍ እውነት አሸንፎ ሌብነትና የአቋራጭ ክብረት እንዲከስሙ ሠርቷል የሙስናና የዝምድና አሠራርንም በድፍረት አውግዟል።

ያልተደረሰበት ከፍታ የተሰኘው የትርጉም ሥራ እና የተለያዩ መፃሕፍት አቅርቦት ሥራው በተለወጠ ግለሰብ ውስጥ የተለወጠ ቤተሰብና የተለወጠ ሀገርን ለማየት ካለ ከፍተኛ ጉጉት ውስጥ የበቀሉ ናቸው። አሁንም ድርጅታችን፥ የመፅሐፍት አቅርቦቱን፥ የዲስኩርና የስልጠና መድረኮችን፥ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በተጠናከረ መልኩ እየሠራ መቀጠል ይፈልጋል። ከዚህ ሌላ ቅንና ትጉህ ሠራተኛ የሆኑ ሠዎች በገጠር በከተማ የሚያብሩበትና ሰውና ሥራ የሚከበርበት፥ዘር ጎሳ፥ ሀይማኖት፥ የፖለቲካ አመለካከት የማይነሳበት፥ የሀገርና የአህጉር ድንበር የሚሻገር “ባለጅ ሥራና ሠራተኞችን አክባሪ ትውልድ ማህበር” የተሰኘ ማህበር መስርቶ በስፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ስለማህበሩ በሚገባ ለመረዳት www.baleij.com የተሰኘውን ድረ ገፅ መጎብኘት ይቻላል። ከሌብነትና አድሎ የፀዱ፥ ሥራና ሠራተኞችን የሚያከብሩ ከሆኑ የማህበሩ አባል ሆነው የባለጅነትን ክብር መቀዳጀት ይገባዎታል።

0
YOUR CART
  • No products in the cart.