ምስጋና

0 minutes, 0 seconds Read

በቅርቡ በርካታ ታዋቂና ድንቅ ደራሲያን ማራኪ ቡክስን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። በግልም በቡድንም ስናነጋግራችሁ አብራችሁን ለመሥራትና ደራሲያንን ተጠቃሚ የማያደርገው ባህላዊው የመጽሐፍ ስርጭት ሥርዓት እንዲሻሻል፤ የገበያውን አድማስ በማስፋት አንባቢውን፥ ደራሲውን እና መጽሐፍ ነጋዴውን እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ ሥርአት በጋራ እንድንገነባ በጎ ፍቃዳችሁን ስላሳያችሁን እናመሠግናለን። ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሚኖርበት ሀገር፥ አምስት ሺህ እና አሥር ሺ ቅጂን መሸጥ እንደተዓምር እየቆጠርን እርስ በርሳችን ስንጠላለፍ ከምንኖር ተረዳድተን አንባቢ ትውልድ እንኮትኩት እና እናልማ ስንላችሁ ትንሹን ጅምራችንን እንደትልቅ ቆጥራችሁ ላለፉት ሁለት አመታት በሂደቱ ውስጥ ለነበራችሁት ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ። ማራኪ ቡክስ በየደረጃው ኢቡክ፥ ኦዲዮ ቡክ እና ፍላጎትን መሠረት አድርገው የሚታተሙ መጽሐፍትን በመላው ሀገሪቱ ለማዳረስ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በቀጣይ ሁሉንም የመፅሐፍ መደብሮች፥ የመጽሐፍ አዟሪዎችን፥ አነስተኛ የህትመት ተቋማትን እና ከደራሲያን ጋር ስምምነት አድርገው ኦዲዮ ቡክ ፕሮዲዩስ የሚያደርጉ ህጋዊ አዘጋጆችን ጭምር ወደሚያሳትፍ ስርዓት ታድጋለች። ደራሲያን መጽሐፎቻቸውን በማራኪ ቡክስ ላይ ጭነው እያንዳንዱን ሽያጭ ይቆጣጠራሉ፤ ሽያጭ ሲከናወን ወዲያውኑ ማን እንደገዛ፥ ምን ያህል እንደተከፈለና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን የያዘ የኢሜል መልዕክት ይደርሳቸዋል። ገቢያቸውንም ያለእጅ ንክኪ፥ ያለምንም መጉላላት በባንክ አካውንታቸው ይሰበስባሉ፤ ኦዲዮ ቡክ አዘጋጅተው በተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ ጭነው ገቢ የሚሰበስቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች ኦዲዮ ቡካቸውን በማራኪ ቡክስ ላይ ጭነው ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላሉ።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0
YOUR CART
  • No products in the cart.