ማራኪ ቡክስ የኢትዮጵያን የመጽሐፍ ስርጭትና ንግድ ሥራ አዲስ ገጽታ የሚያላብስ  አሠራር ጀመረ

0 minutes, 0 seconds Read

በኢትዮጵያ ውስጥ ደራሲ ወይም ተርጓሚ ሆኖ መጽሐፍ መጻፍ አበረታች አይደለም፤ በተለይም  ከህትመቱ ጀምሮ እስከስርጭቱ ያለው አጠቃላይ ሂደት ብዙዎች ሊያስቡት እንኳን የማይፈልጉት አታካች ጉዳይ እንደሆነ ተደጋግሞ ይነገራል። ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የህትመት ግብዓት ዋጋ ከ500 እስከ 600 % መጨመሩ ደግሞ ችግሩን የበለጠ አብብሶታል። 

ለህትመት የሚጠየቀው ገንዘብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በመጨመሩ ማሳተም አልቻልንም፤ መጽሐፋችንን አሳትመን በምን ዓይነት መንገድ እንደምናሰራጨው ተቸገርን፥ መጽሐፋችን ታትሞና ተሰራጭቶ ከገበያ ላይ ቢያልቅም ሊከፈለን ስላልቻለ ዕዳውስጥ ገብተናል። ከመጽሐፍ አከፋፋዮች ጋር ባለመግባባታችን በከፍተኛ ወጪ ያሳተምነው መጽሐፍ ተከምሮ ቀረ፥ እና አንባቢ የለም የሚሉ ቅሬታዎች ተደጋግመው ይደመጣሉ።  5000 እና 10000 ቅጂ መሸጥ እንደተዓምር የሚቆጠርበት ጊዜም ብዙ ነው። 

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ መጽሐፍትን በማቅረብ የሚታወቀው ባለጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ በእህት ኩባንያው ማራኪ ቡክስ አማካኝነት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም ተያያዥ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል አዲስ አሠራር በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። አዲሱ የማራኪ ቡክስ ኦንላይን የመጽሐፍ መሸጫ ሥርዓት ደራሲዎችንና አሳታሚዎችን በቀጥታ የሚያሳትፍ ሲሆን ደራሲዎች ወይም አሳታሚዎች በድረገፁ ላይ ራሳቸው የግል መደብር በመክፈት መጽሐፎቻቸውን መጫን እና ዋጋውን ራሳቸው በመተመን መሸጥ የሚችሉበት ነው፤ ከተደራሲያን ጋርም በቀጥታ ለመወያየት፥ ሽያጫቸውን ለመከታተልና ሁሉንም እንቅስቃሴ በየደቂቃው ለመቆጣጠር የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር ደራሲያኑ ወይም አሳታሚዎች ክፍያቸውን ያለምንም ውጣውርድ በቀጥታ በባንክ አካውንታቸው እንደሚያገኙም ተጠቅሷል። 

በዚህ ሥርዓት ላይ መጽሐፍት ብቻ ሳይሆኑ መጽሔቶችንና ጋዜጦችንም ማዳረስ እንደሚቻል፤  እንዲሁም መጻሕፍትን በመተረክ በተበታተነ መልኩ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያቀርቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች በማራኪ ቡክስ ላይ መደብራቸውን በመክፈት ቅጂዎቻቸውን እንዲጭኑ እና ካጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 10 በመቶውን የሚሸፍኑትን ማየት የተሳናቸውን ዜጎችና በሥራ ብዛት የማንበቢያ ጊዜ የቸገራቸውን ሁሉ ተደራሽ እንዲያደርጉ ተጋብዛዋል። 

ማራኪ ቡክስ በኢትዮጵያም ሆነ በሁሉም የዓለም ሀገራት የሚኖሩ አንባቢያን በቀላሉ በዶላርም ሆነ በብር ግዢ መፈፀም የሚችሉባቸው የኦላይን የክፍያ አማራጮች የተካተቱበት ሲሆን፥ ለህትመት ግብዓት ዋጋ የሚወጣውን የውጪ ምንዛሪ በማስቀረት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጪ ከሚኖሩ አንባቢያን የውጪ ምንዛሪን በመሰብሰብ የሀገር ዕድገትን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል። በማራኪ ቡክስ ኢቡክ፥ ኦዲዮ ቡክ እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ህትመት (ቡክ ኦን ዲማንድ) አገልግሎት በመስጠት የመጽሐፍን ተደራሽነት ከፍ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል። 

የማራኪ ቡክስ የኦንላይን የመጽሐፍ መሸጫ ሥርዓት ደራሲያንን፥ አሳታሚዎችን እና እንባቢያንን እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር መጻሕፍትን በአነስተኛ ዋጋ በማቅረብ የአንባቢያንን ቁጥር በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል። 

ማራኪ ቡክስ ሙሉ በሙሉ መሠረቱን ኢትዮጵያ ውስጥ በማድረግ በህገሪቱ ህጎች መሠረት የተቋቋመ ድርጅት ስለሆነ በደራሲያን እና በሽያጭ ስርዓቱ መካከል ከፍተኛ መተማመን እና ተጋግዞ መሥራትን ያበረታታል ተብሎም ይጠበቃል።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0
YOUR CART
  • No products in the cart.