ማራኪ ቡክስ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን እያገኘች ነው

0 minutes, 0 seconds Read

ውድ ደራሲያን እና አንባቢያን ከማራኪ ቡክስ ጋር ስለሆናችሁ በጣም እናመሰግናለን። ማራኪ ቡክስ ከመፃፍ፥ ከማንበብ፥ ከመሸጥ እና ከመግዛት በላይ በመጽሐፍ ውስጥ ሌላ ግብ አለ ትላለች። ይህ ግብ ደግሞ የአንድ ግለሰብ፥ የአንድ ብሔር፥ የአንድ ሀገር ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ በዓለም ላይ ያሉና የነበሩ ፖለቲከኞች ታሪካችንን የሚነግሩን ለራሳቸው እንዲመቻቸው በመሆኑ አሁን ያለው የተዛባ የሰው ለሰው ግንኙነት ሊፈጠር ችሏል። ይህ ችግር የሚፈታው ደግሞ ሁሉም የግል የውድቀትም ሆነ የስኬት ታሪኩን በአንድም በሌላም መንግድ ሲያጋራ፥ ያ ደግሞ ተሰንዶ ለትውልድ ሲያልፍ ቀስ በቀስ ችግሮች እየተፈቱ የሰው ለሰው ግንኙነቱም እየተጠናከረ፥ የዓለም ህዝቦች አንዱ ለሌላው ግብዓት የሚሆን እንጂ ስጋት እንዳልሆነ የሚገነዘቡበት ጊዜ ይመጣል።

ይህን የማራኪ ቡክስ ትልቅ ዓላማ የተገነዘቡ የሚዲያ ተቋማት እና የሚዲያ ባልሞያዎች ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ሽፋን እየሰጡ ይገኛሉ።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ማራኪ ቡክስ በይፋ ሥራ ከጀመረች ጊዜ አንስቶ  ጋዜጠኛ ስዩም ፍቃዱ፥ ብሥራት ራዲዮ፥ ሁሉ አዲስ ራዲዮ ፕሮግራም፤ ጋዜጠኛ ሮቤራ አምሳሉ ኢትዮ ኤፍኤም፥ ክቡራን እና ክቡራት የራዲዮ ፕሮግራም፥ ጋዜጠኛ ዮናስ ክብረት ኢትዮ ኤፍ ኤም፥ ዘናጭ የራዲዮ ፕሮግራም፤ ጋዜጠኛ ውብሸት አሠፋ፥ ትርታ ራዲዮ እልፍኝ የራዲዮ ፕሮግራም፥ ጋዜጠኛ እና አርቲስት ቴዎድሮስ ተሰማ፥ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1፥ ደመራ የራዲዮ ፕሮግራም፤ ጋዜጠኛ ሽመልስ በቀለ ሽመልስ፥ ሸገር ኤፍ ኤም፥ አደረች አራዳ የራዲዮ ፕሮግራም፤ ልፋታችንን አጢናችሁ፥ ውጤታችንን አድንቃችሁ፥ ራዕያችንን ተጋርታችሁ ሰፋፊ የአየር ሰዓት በመመደብ ስለማራኪ ቡክስ የተደራጀ የራዲዮ ፕሮግራም ስለሠራችሁልን እና ወደፊትም እንደምታግዙን ቃል ስለገባችሁ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0
YOUR CART
  • No products in the cart.