ማራኪ ቡክስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ኦንላይን ኢቡክ ሽያጭ ሊጀምር ነው።

0 minutes, 0 seconds Read

የማራኪ ቡክስ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛና መምህር ነቢዩ ተፈራ በኢትዮጵያ የሚታየውን የመጽሐፍ ህትመት ዋጋ፥ የስርጭት ስርዓት ኋላ ቀርነት ደራሲያንና አንባቢያንን የማያበረታታ መሆኑን በመግለፅ ድርጅቱ ማራኪ ቡክስ ችግሩን ለመፍታት የጀመረው ጥረት ፍሬ ማፍራት መጀመሩን አስታውቋል። በቅርቡ ይፋ በሆነ መረጃ አብዛኛው የስልክ ተጠቃሚ ኢ ቡክ ለማውረድና ለማንበብ የሚያስችል ዘመናዊ ስልክ ባለቤት መሆኑ ተገልጿል። ስለዚህ በአነስተኛ ዋጋ ኢ ቡክ በመሸጥ ትውልዱ የንባብ ልምዱን እንዲያዳብር እና የተሻለ ዜጋ እንዲሆን ማገዝ ይቻላል። ሂደቱም የውጪ ምንዛሪ በማምጣት፥ ለወረቀት እና ለህትመት ግብእቶች የሚወጣውን የውጪ ምርዛሪ በመቀነስ፥ እንዲሁም የመጽሐፍ ዋጋን ተመጣጣኝ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሚታ እንዳለው ተነግሯል። ማራኪ ቡክስ ከአቢሲኒያ ባንክ፥ ከቴሌ ብር እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ውል በመፈራረም የክፍያ ሥርዕቶቹን ከመጽሐፍ መሸጫ ሥርዓቱ ጋር በማቀናጀት ግብዩቱን ቀላል ለማድረግ ጥርት እያደረጉ መሆኑን ተናግራዋል።

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0
YOUR CART
  • No products in the cart.